እንቁጣጣሽ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🌼✨ እንኳን ለ፪ሺህ፲፱ (2019) ዓመተ ምሕረት አዲሱ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ! ✨🌼
“የምሕረት ዓመትን ይሰብክ ዘንድ ላከኝ።” (ሉቃስ 4:19)
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የሆናችሁ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን እንደምን አላችሁ፤
በመጀመሪያ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብሩህ ብርሃን፤ ከአሮጊው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን፤ ከዓመተ ኩነኔ ወደ ዓመተ ምሕረት ያሸጋገረን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን!
እንኳን ከባረከንና ከቀደሰን የዘመነ ማርቆስ ፍጻሜ አደርሶ፤ ወደ አዲሱ ዘመነ ሉቃስ በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አሸጋገራችሁ፤ አሸጋገረን።
🇪🇹 የ2019 ዓ.ም አዲሱ ዓመት የሰላምና የፍቅር፣ የደስታና የተስፋ፣ የጤናና የበረከት ዓመት ይሁንልን።
የተጣላ የሚታረቅበት፣ የተራራቀ የሚቀራረብበት፣ የታመመ የሚድንበት፣ የተራበ የሚጠግብበትና የተነፋፈቀ የሚገናኝበት ይሁንልን።
የተዘጋ በር የሚከፈትበት፣ የጠፋ ተስፋ የሚመለስበት፣ የተሰበረ ልብ የሚጽናናበትና የተቸገረ እጅ የሚያገኝበት የበረከት ዘመን ያድርግልን።
🙏 አሜን
መልካም አዲስ ዓመት! 🌼✨
