Skip to content
በቼክ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ የቅዱስ ሚካኤል ማህበር
  • ቀዳሚ ገፅ
  • ስለ እኛExpand
    • ማህበራችን
    • እምነታችን
    • አባል ይሁኑ
  • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
  • መርሐ ግብርExpand
    • ጠቅላላ መርሐ ግብሮች
    • ሥርዓተ አምልኮ
    • አጽዋማት
    • በዓላት
  • መንፈሳዊ መገልገያ
  • ያግኙን
ይለግሱ
አማርኛ
  • English English
  • Čeština Čeština
አማርኛ
  • English English
  • Čeština Čeština
በቼክ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ የቅዱስ ሚካኤል ማህበር

እምነታችን

እምነታችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛይቱ ሃይማኖት (ኦርቶዶክስ)፣ ቀኖና፣ ሥርዓትና መንፈሳዊ ትውፊት ላይ የተመሠረተ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ሐዋርያዊት እንደመሆኗ መጠን፤ ሕይወቷና መዋቅሯ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በቅዱስ ትውፊት፣ በቅዱስ ቅዳሴ፣ በጸሎት፣ በሰባቱ የአጽዋማት ሥርዓቶች፣ በንስሐና በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ላይ የጸና ነው።

ቤተ ክርስቲያናችን በአንድነት በሦስትነት (በመለኮት አንድ፣ በአካል ሦስት) በሆኑ በቅድስት ሥላሴ — በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ — ታምናለች። እንዲሁም ስለ ሰው ልጅ ድኅነትና ቤዛነት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ (ሰው ሆኖ) የመጣውን፣ የተሰቀለውን፣ የሞተውን፣ የተቀበረውን፣ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ የተነሣውንና ዳግመኛ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በክብር የሚመጣውን ጌታችንን፣ መድኃኒታችንንና አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ታመልካለች።

“ተዋሕዶ” የሚለው ቃል የሃይማኖታችን ዓምድና መሠረት ነው። እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትና ትስብእት (ሰውነቱ) ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለወጥ፣ ያለ መለየትና ያለ መከፋፈል አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሆኑበትን ረቂቅ የነገረ መለኮት ምሥጢር (ምሥጢረ ሥጋዌን) ያመለክታል። ይህ እምነት ለቤተ ክርስቲያናችን ሕይወት፣ ሥርዓትና መንፈሳዊ ጉዞ ዋነኛ መሠረት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንፈሳዊ ሕይወት በጸሎት፣ በቅዱስ ቅዳሴ፣ በጾም፣ በንስሐ፣ በበዓላት አከባበር፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ እንዲሁም በፍቅርና በትሕትና ላይ የተመሠረተ ነው። ምእመናን በኦርቶዶክሳዊት እምነት እንዲጸኑ፣ በቅዱስ ሥነ ምግባር እንዲመላለሱና በቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲበረቱ ታስተምራለች።

የእመቤታችን፣ የቅዱሳን መላእክትና የጻድቃን ክብር

በቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓት መሠረት፣ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ እና የከበረ ቦታ (የጸጋ ስግደት) እንሰጣለን። እርስዋ የጌታችን እናትና የፍጥረት ሁሉ አማላጅ በመሆንዋ “ወላዲተ አምላክ” ብለን እናከብራታለን። በተጨማሪም፣ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቆመው ዘወትር የሚያመሰግኑትን፣ የሰውን ልጅ የሚጠብቁትንና የሚያማልዱትን ቅዱሳን መላእክትን፣ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብለው ዓለምን የናቁ፣ ደማቸውን ያፈሰሱ እና ተጋድሎ ያደረጉ ቅዱሳንን፣ ጻድቃንንና ሰማዕታትን እናከብራለን፤ በጸሎታቸው፣ በምልጃቸውና በቃል ኪዳናቸውም እናምናለን።

ቅዱስ ሚካኤል — ጠባቂያችንና አማላጃችን

ማኅበራችን በዋናው መልአክ በቅዱስ ሚካኤል ስም የተሰየመ እንደመሆኑ መጠን፣ ለሊቀ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤል የሚገባውን የጸጋ ስግደትና አክብሮት በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት እናቀርባለን። ቅዱስ ሚካኤል በቅዱሳት መጻሕፍትና በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ውስጥ የእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ፣ የቅዱሳን መላእክት አለቃ፣ የምእመናን ረዳት፣ ነፃ አውጪና ጠባቂ ነው።

በቅዱስ ሚካኤል ስም መሰባሰባችን ለእኛ የመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ የጽናት፣ የታማኝነትና የቅን አገልግሎት ምልክት ነው። በእግዚአብሔር ፊት በሚያቀርበው የቅዱስነቱ ምልጃና ጸሎት፤ ልዑል እግዚአብሔር ማኅበራችንን፣ ምእመናንን፣ ቤተሰቦችንና ሕፃናትን ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲጠብቅልንና እንዲባርክልን ዘወትር እንማጸናለን።

እምነታችን በቃል ብቻ የሚገለጥ ሳይሆን በጸሎት፣ በምግባር፣ በማኅበረሰብ ፍቅር፣ በሕብረትና በትሕትና የሚኖር እውነተኛ የክርስትና ሕይወት ነው። ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን በትክክለኛው ሥርዓት ለመማር፣ ለመጠየቅ እና በመንፈሳዊ ሕይወት አብሮ ለማደግ የሚፈልጉትን ሁሉ በፍቅርና በደስታ እንቀበላለን።

በፕራግ ቼክ ሪፐብሊክ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና በሃይማኖት መበርታት ለሚፈልጉ ሁሉ መንፈሳዊ ቤት

info@stmichaeleotc.cz

ማህበራችንን ያጠናክሩ

© 2026 በቼክ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ የቅዱስ ሚካኤል ማህበር

Scroll to top
  • ቀዳሚ ገፅ
  • ስለ እኛ
    • ማህበራችን
    • እምነታችን
    • አባል ይሁኑ
  • መንፈሳዊ አገልግሎቶች
  • መርሐ ግብር
    • ጠቅላላ መርሐ ግብሮች
    • ሥርዓተ አምልኮ
    • አጽዋማት
    • በዓላት
  • መንፈሳዊ መገልገያ
  • ያግኙን
ይፈልጉ