በፕራግ የቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበር ይፋዊና ሕጋዊ ዕውቅና አገኘ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
በቼክ ሪፐብሊክ በፕራግና በአካባቢዋ የምትኖሩ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ፤
“እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፥ እኛም ደስ አለን።”
መዝ ፻፳፭፥፫
በፕራግ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን መሠረት ለመጣል ይረዳን ዘንድ፣ ማኅበራችን በቼክ መንግሥት ዘንድ ይፋዊና ሕጋዊ ዕውቅና (spolek) ማግኘቱን በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ እናበስራችኋለን።
ይህን ታሪካዊ ምዕራፍ ሊመዘገብ እንዲችል ላደረገልን ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን። ለዚህ የተባረከ ስኬት የተሳተፋችሁ፣ የደገፋችሁና የተባበራችሁ በሙሉ በቤተክርስቲያን ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ለቀጣዩም የቤተክርስቲያን ምሥረታ ጉዟችን እግዚአብሔር ኃይልን፣ አንድነትንና ብርታትን ይስጠን።
