« All መርሐ ግብሮች

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ

Loading መርሐ ግብሮች
  • This መርሐ ግብር has passed.

June 27 @ 9:00 – 13:00

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
«የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።» (መዝ. ፴፫፥፯)

ክቡራንና ክቡራት የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች፣ በቼክ ሪፐብሊክ በፕራግና በአካባቢው የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ፦

የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር አምላካችን ፈቃዱ ሆኖ፣ በፕራግና በአካባቢው ለምትገኙ ምዕመናን ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።
የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እንድንመገብና የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን በታላቅ አክብሮት ተጋብዘናል።

የዕለቱ ክቡራን ተጋባዥ መምህራን

በዕለቱ የእግዚአብሔርን ቃል ይዘውልን የሚቀርቡና ጉባኤውን በጸሎትና በትምህርት የሚባርኩ ታላላቅ አባቶችና መምህራን ተገኝተዋል፦

  1. ክቡር አባታችን መላከ ሣዕል ቆሞስ አባ ወልደዮሐንስ
  2. ክቡር ዶክተር ቀሲስ ዘላለም (ከናይሮቢ፣ ኬንያ)

በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ሁላችሁም ከነቤተሰቦቻችሁ ተገኝታችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጠውን ረድኤትና በረከት እንድትሳተፉ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

አድራሻ

Barikád 1520/1
Praha, Praha 3-Žižkov 130 00 Czech Republic
+ Google Map